Thursday, November 28, 2024
spot_img

ሕወሓት በጋሸና እና በሰሜን ሸዋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ዜጎችን በጅምላ መጨፍጨፉን መንግሥት አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ኅዳር 27፣ 2014 ― ሕወሓት ከሰሞኑ በአማራ ክልል ጋሸና እና በሰሜን ሸዋ በምትገኘው አንጾኪያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ዜጎችን በጅምላ መጨፍጨፉን መንግሥት አስታውቋል፡፡

በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ የሆኑት ሰላማዊት ካሳ እንደገለጹት፣ ‹‹በሁሉም ግንባሮች ከፍተኛ ሽንፈትን እያስተናገደ›› ይገኛል ያሉት የሕወሓት ኃይል፣ ተሸንፎ በሚወጣባቸው አካባቢዎች ‹‹ለመስማት የሚዘገንኑ ወንጀሎችን በንጹሃን ላይ ፈጽሟል›› ብለዋል፡፡

እነዚህ ድርጊቶች የቡድኑን ትክክለኛ ማንነት በግልጽ ያወጡ ናቸው ያሉት ሰላማዊት፣ በጋሸናና በሰሜን ሸዋ አንጾኪያ ከሰሞኑ እንኳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎችን በጅምላ መጨፍጨፉን የሚያረጋግጡ መረጃዎች መውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡  

ነገር ግን ‹‹በአማራና በአፋር ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት እየፈጸመ ያለው ይህ የሽብር ቡድን ሆኖ ሳለ ትክክለኛውን ሐቅ ማየት የማይፈልጉ አካላት ግን ዛሬም በእነዚህ ክልሎች ውስጥ ቡድኑ ስለሚፈጽማቸው ወንጀሎች ማንሳት አይፈልጉም›› ሲሉም አክለዋል፡፡

ወይዘሮ ሰላማዊት አያይዘውም ለሰብአዊ መብት ቆመናል የሚሉት አለም አቀፍ ተቋማት ይህን የቡድኑን ወንጀሎች ››እንደ እስከዛሬው ሁሉ እንዳላየ እንደማያልፉት እምነታችን ነው›› ብለዋል፡፡

አንድ ዓመት በተሻገረው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጦርነት ከሰሞኑ ተባብሶ ቀጥሎ የፌዴራል መንግስት ሕወሓት ድንበር ተሻግሮ የያዛቸውን በርካታ የአማራ እና አፋር ክልል አካባቢዎች ማስለቀቁን አስታውቋል፡፡   

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img