Thursday, November 28, 2024
spot_img

የመንግሥታቱ ድርጅት አቋርጦት የነበረውን የመቐለ በረራውን ዳግም ጀመረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 22፣ 2014 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከጥቅምት 12፣ 2014 ጀምሮ አቋርጦት የነበረውን የመቐለ በረራ ከባለፈው ሳምንት አንስቶ በድጋሚ ማስጀመሩን የድርጅቱ የሰብአዊ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ አቋርጦ የነበረው ጥቅምት 12፣ 2014 ወደ ከተማዋ የተጓዘ አውሮፕላን ማረፍ ሳይችል ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ ነበር፡፡

የሰብአዊ ማስተባበሪያ ቢሮው ባወጣው ሳምንታዊ ሪፖርት እንደገለጸው፣ የበረራውን መቀጠል ተከተሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ ሠራተኞችን ማዘዋወር ተችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለሥራ የሚያስፈልገውን የተወሰነ መጠኝ ያለው ጥሬ ገንዘብ ማዘዋወር እንደተቻለም የድርጅቱ የሰብአዊ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img