Saturday, October 5, 2024
spot_img

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለዶ/ር እሌኒ ዘውዴ ገብረመድኅን ሰጥቶ የነበረውን የክብር ዶክትሬት ሠረዘ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 21፣ 2014 ― የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ለዶ/ር እሌኒ ዘውዴ ገብረመድኅን ሰጥቶ የነበረውን የክብር ዶክትሬት መሠረዙን አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 29፣ 2005 የሰጠው የክብር ዶክትሬት እሌኒ የኢትዮጵያ ምርት ገበያን በማቋቋምና በመምራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ያበረከተው ነበር።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በወቅቱ የክብር ዶክትሬቱን የሰጣቸው የህብረተሰቡን አኗኗር እና የሀገሪቱን የውጭ ንግድ ስርዓት እንዲሻሻል ባበረከቱት መልካም አስተዋጽኦ እና ለወደፊቱም በተሰጣቸው የክብር ዶክትሬት ልክ ሀገሪቱን ያለአድሎና በእኩልነት እንዲያገለግሉ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ አምባሳደር ሆነው እንዲያገለግሉ መሆኑን አስታውሷል።

ሆኖም ዶ/ር ኢሌኒ ሰሞኑን የዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ማዕከል ተብሎ ይጠራ በነበረው ድርጅት አማካኝነት በድብቅ በተዘጋጀ የበይነ መረብ ስብሰባ ላይ ሞያዊነትን ያልጠበቀ፣ አድሏዊ፣ የአንድን ቡድን ፍላጎት ብቻ ያንጸባረቀ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን ዋና ዋና እሴቶች የሚፃረር ያለውን ሀሳብ በማራመዳቸው ዩኒቨርሲቲው የሰጠውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በድጋሚ ሲያጤን እና ሲመረምር ቆይቷል ብሏል።

በዚህም መሠረት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ለዶ/ር ኢሌኒ ዘውዴ ገብረ መድኅን ሰጥቶት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንዲሰረዝ መወሰኑን አስታውቋል።

ዶክተር እሌኒ ገብረመድኅን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ማዕከል ባዘጋጀውና በበይነ መረብ ያደረጉት ምስጢራዊ ውይይት አፈትልኮ መውጣቱን ተከትሎ በተመሳሳይ ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤት እንደተነሱ መነገሩ አይዘነጋም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img