Tuesday, November 12, 2024
spot_img

አቶ ጌታቸው ረዳ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የሰጡትን መግለጫ አጣጣሉት

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሚያዝያ 18፣ 2013 ― ከፌዴራል መንግሥት ጋር ጦርነት የገባውን የሕወሃት ቡድን ከሚመሩት መካከል እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ጌታቸው ረዳ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ‹የሕወሃት ኃይሎች ጋንታ የላቸውም› ማለታቸው ስህተት መሆኑን ገልጸው አጣጥለውታል፡፡ ከየት አካባቢ እንደተቀዳ ባልታወቀ ነገር ግን ትግራይ ሚዲያ ሐውስ በተባለ የኦንላይን ሚዲያ በተሠራጨ አጭር ቪድዮ አቶ ጌታቸው ረዳ ብርሃኑ ጁላ ይህን መግለጫ በሰጡበት ሰአት ‹‹የ33ኛ ክፍለ ጦር አንድ ሜካናይዝድ ብርጌድ ሰአታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተደምስሷል፣ ይህን ያውቃል›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ በሌላ በኩል አቶ ጌታቸው ረዳ የአገር መከላከያ ሰራዊት የሠራዊት ግንባታ ዋና አስተባባሪ ስለሆኑት ባጫ ደበሌን በሚመለከትም የተናገሩ ሲሆን፣ የሕወሃት አመራሩ ‹‹ባጫ ወታደር አይደለም›› ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ የኢፌዴሪ የአገር መከላከያ ሠራዊት ሕወሃትን አስመልክቶ በሰጠው የመጨረሻ መግለጫው ከሕወሃት ሰዎች መካከል የሆኑ ‹‹ሐሰተኛ የሌላ ክልል መተወቂያ በማውጣት ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ለመሸሽ ሙከራ ሲያደርጉ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አሳውቆ ነበር፡፡ የአገር መከላከያ ሰራዊት የሠራዊት ግንባታ ዋና አስተባባሪ የሆኑት ባጫ ደበሌ እንደተናገሩት ከሆነ የዚህ ድርጊት ዋና አላማ ‹‹እነዚህን አባላት ወደ ሱዳን በማሸሽ ከዚያ ሆኖ አገር ውስጥ ያሉትን ታጣቂ ኃይሎች በሽምቅ ውጊያ በማሰማራት አገር ለመበጥበጥ የታቀደ ነበር››፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img