Wednesday, November 27, 2024
spot_img

በትግራዩ ጦርነት የተፈጸሙ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የተቋቋመው ግብረ ኃይል ሥራ መጀመሩ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 21፣ 2014 ― መንግሥት በትግራዩ ጦርነት የተፈጸሙ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የተቋቋመው ግብረ ኃይል ሥራ መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡

ፍትህ ሚንስቴር በትዊተር ገጹ ባሰራጨው መረጃ እንደገለጸው፣ ግብረ ኃይሉ በጦርነቱ በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በጋራ አጥንተው ያቀረቧቸውን ምክረ ሃሳቦች ለመተግበር የሚያስችለውን ስትራቴጂ እና የድርጊት መርሃ ግብር አጽድቋል።

ምርመራና ክስን፣ ስደተኞችንና ተፈናቃዮችን፣ የጾታ ጥቃቶችን እና ሐብት ማፈላለግን የሚመለከቱ አራት ኮሚቴዎች ያዋቀረው ግብረ ኃይሉ፣ ሥራውን የሚከታተል ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤትም ያቋቁማል ተብሏል።

የግብረ ኃይሉ ሥራ ከትግራይ ክልል በተጨማሪ በአማራ እና አፋር ክልል የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንም ያካትታል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img