Sunday, October 6, 2024
spot_img

ጋጮ ባባ ወረዳ በደረሰ ናዳ 3 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሚያዝያ 18፣ 2013 ― የጋጮ ባባ ወረዳ የአደጋ ስጋት አመራር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢዮብ ዳርጻ እንደገለፁት በወረዳው ላካ ቀበሌ ቅዳሜ ሚያዝያ 16፣ 2013 ከሌሊቱ 8 ሠዓት አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ በደረሰ የናዳ አደጋ የ1 ወንድ እና የ2 ሴቶች ሕይወት ተነጥቋል፡፡ በተጨማሪም በአደጋው 3 መኖሪያ ቤቶች ከሙሉ ንብረታቸው ጋር የወደሙ መሆናቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ 8 የቤት እንስሳት በአደጋው ሞተዋል ብለዋል፡፡ አክለውም በ2 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ ያለ ቋሚ እና ጊዜያዊ ሰብል ላይ ጉዳት ደርሷል።የጋሞ ዞን እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አንደኛ ሽናሌ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የመጠለያ ሸራ፣ የአልባሳት እና የቤት ቁሳቁድ ድጋፍ ተደርጓል ነው ያሉት። አደጋው በደረሰበት አከባቢ ተጨማሪ 10 ቤተሰብ ለአደጋ ስጋት ተጋላጭ በመሆናቸው መለየቱን ገልጸው፣ ለተጎጂዎች ተጨማሪ የመጠለያ እና የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚደረግ መናገራቸውን ከጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img