Sunday, October 6, 2024
spot_img

በሰሜን ሸዋ ግጭት 200 ያክል ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሚያዝያ 18፣ 2013 ― ከሳምንት በፊት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ውስጥ በተከሰተው ግጭት እስከ 200 የሚደርሱ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ሬውተርስ የዜና ወኪል አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም ኃላፊ አቶ እንዳለ ኃይሌ እንደተናገሩት ‹‹ከተፈናቀሉ ሰዎች ያገኘነውን መረጃ መሠረት አድርገን እስከ 200 የሚደርሱ ሰዎች ከሁለቱም ዞኖች ሳይሞቱ አይቀሩም›› ሲሉ ነግረውኛል ብሎ ነው የዜና ወኪሉ የዘገበው፡፡ኃላፊ ጨምረውም ይህ የተጠቀሰው የሞቱ ሰዎች አሐዝ የበለጠ ማረጋገጥ እንደሚፈልግም አመልክተዋል።በቅርብ ጊዜ በተከሰተው ጥቃት ክፉኛ ከተጎዱት አካባቢዎች መካከል ዋነኛዋ በሆነችው በአጣዬ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ቤቶች ውስጥ ከ20 እስከ 25 በመቶ የሚሆኑት በእሳት መጋየታቸውን አቶ እንዳለ ተናግረዋል።በተጨማሪም ከሰሜን ሸዋ ዞን 250 ሺሕ የሚጠጉ ሰዎች እንዲሁም 78 ሺሕ የሚሆኑ ደግሞ ከኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ጥቃቶቹን የሚያወገወዙ በርካታ ሠልፎች ሲደረጉ መሰንበታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img