Sunday, September 22, 2024
spot_img

የቱርክ ኤምባሲ ሠራተኞች ከአገር ለቀው መውጣታቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ኅዳር 18፣ 2014 ― በአዲስ አበባ የሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ ሠራተኞች ከአገር ለቀው መውጣታቸው ተሰምቷል፡፡ ኤምባሲው ባሳለፍነው ሰኞ ኅዳር 13፣ 2014 ባወጣው መግለጫ የአገሪቱ ዜጎች ከወቅታዊ የኢትዮጵያ ጸጥታ ሁኔታ ጋር በተገናኘ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ መስጠቱ አይዘነጋም፡፡

የዚህ ኤምባሲ የቪዛ ጉዳዮችን የሚመለከተው ክፍል ጨምሮ የኤምባሲው ሌሎች አገልግሎቶችን የሚሰጡ ክፍል ሠራተኞች ከአገር ለቀው መውጣታቸው ነው የተሰማው፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጦርነት መባባሱን ተከትሎ ከቀናት በፊት የአሜሪካ መንግሥት እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ ሌሎችም አገራት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዜጎቻቸውን እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጥተው ነበር፡፡

ከአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም ተጨማሪ ስዊድን፣ ጀርመን፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ደቡብ ኮሪያ ለዜጎቻቸው ኢትዮጵያን ለቃችው ውጡ የሚል ማሳሰቢያ የሰጡ ቢሆንም፣ መንግሥት ግን እነዚህ አገራት ያስለላለፉት ዜጎቻቸውን ውጡ የሚል ማሳሰቢያ የተጋነነ ነው ሲል አጣጥሎታል፡፡

በአንጻሩ በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩስያ ኤምባሲ ከተማዋ የተረጋጋች በመሆኗ የተለመደ ሥራችንን ቀጥለናል ሲል ሐሙስ ኅዳር 16፣ 2014 ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኤምባሲው በአዲስ አበባ ከተማ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ በመሆኑ ሠራተኞቹንና ቤተሰቦቻቸውን የማስወጣት ዕቅድ እንደሌለውም ነው ያስታወቀው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img