Saturday, November 23, 2024
spot_img

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኬንያው ፕሬዝዳንት ጋር በኢትዮጵያ ጋር በስልክ መምከራቸውን አሳወቁ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ኅዳር 18፣ 2014 ― የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶንዮ ብሊንክን ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በኢትዮጵያ ጋር በስልክ መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ብሊንክን ከኡሁሩ ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ፣ ለምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላም እና ጸጥታ ስጋት መሆኑን የጠቀሱት የኢትዮጵያ ወታደራዊ ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ፣ ሁለቱ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ግጭቱ ለተጎዱ አካባቢዎች ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት እንዲደርስ መስማማታውን አስታውቋል፡፡ አክለውም ሁሉንም ያማከለ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲደረግ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል ነው የተባለው፡፡

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶንዮ ብሊንክን ከቀናት በፊት ወደ ኡሁሩ አገር ኬንያ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና በሕወሓት መካከል የሚካሄደውን ውይይት ለማሸማገል እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው የሚነገርላቸው ብሊንክንን ያስተናገዱት ኡሁሩ፣ የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከመቀበላቸው ቀድሞ ባለው ቀን ወደ ኢትዮጵያ አቅንተው ፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን አግኝተው ነበር፡፡

ኡሁሩ ኬንያታ ወደ አገራቸው ተመልሰው አንቶንዮ ብሊንክንን ካስተናገዱ በኋላ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ የሚሉ ዘገባዎች ወጥተው የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ስለማቅናታቸው በይፋ የተነገረ ነገር የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img