Friday, November 22, 2024
spot_img

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፈው መታወቂያ እየሰጡ ነው ያላቸውን የጤና ተቋማት አስጠነቀቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ኅዳር 18፣ 2014 ― የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመላ አገሪቱ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተላልፈው መታወቂያ እየሰጡ መሆናቸውን ደርሼባቸዋለሁ ያላቸውን የጤና ተቋማት አስጠንቅቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ባወጣው መግለጫ ሥማቸውን ያልጠቀሳቸው የጤና ተቋማቱ እያደረጉት ነው ያለውን ይህን ተግባር ‹‹ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በቀጥታ የሚቃረን እና ሰላም የማስከበር ስራችን ላይ እንቅፋት የሚፈጥር›› ብሎታል፡፡

በመሆኑም ከነዚህ የጤና ተቋማት በተጨማሪ ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅት የትኛውንም አይነት መታወቂያ እንዳይሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር አሳስቧል፡፡

በሌላ በኩል የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት የአዲስ አበባን ነዋሪ የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከተከራየበት ቤት ማስለቀቅ እንደማይቻል ውሳኔ ማተላለፉን ያስታወሰው የከተማ አስተደዳሩ፣ ውሳኔው ለቀጣይ ሶስት ወራት ባለበት እንዲጸና ብሏል፡፡

በመሆኑም ከትላንት ኅዳር 17፣ 2014 ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ወራት የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስለቀቅ ፈጽሞ ክልክል መሆኑን አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img