Wednesday, November 27, 2024
spot_img

በደቡባዊ አፍሪካ የተገኘ አዲስ የኮቪድ ዝርያ ስጋት ቀሰቀሰ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ኅዳር 17 2014 በደቡባዊ አፍሪካ በሚገኙ አገራት የተገኘ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ አዲስ ስጋት መቀስቀሱ ተነግሯል፡፡

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በደቡባዊ የአፍሪካ አገራት መታየቱ ሲገልጽ፣ በዓይነቱ የተለየ፣ በመዛመት ፍጥነቱ የከፋ ነው ተብሏል፡፡

ባለሞያዎች ይህን አዲስ ዝርያ B.1.1.529 በሚል የጠሩት ሲሆን፣ እስከዛሬ ከታዩ ዝርያዎች ሁሉ የከፋው ነው ተብሎለታል፡፡ በዚህ ዝርያ ተይዘው የተገኙ 59 ሰዎች ብቻ ሲሆኑ፣ እነሱም በደቡብ አፍሪካ፣ በሆንግ ኮንግና በቦትስዋና ውስጥ ነው ሪፖርት የተደረጉ መሆናቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

ስለ ዝርያው ለጊዜው ብዙ እንደማይታወቅና ገና እየተጠና እንደሆነም የተነገረ ቢሆንም፣ ዝርያው ራሱን የሚያባዛበት መንገድ አስደንጋጭ እንደሆነና ዴልታ ከተባለው ዝርያ እጥፍ ራሱን እንደሚያባዛ ተጠቁሟል፡፡

ለአዲሱ ዝርያ እስካሁን የተሰሩ ክትባቶች መከላከያ ይሆናሉ አይሆኑም የሚለውም ገና የሚጠና ስለመሆኑም ነው የተነገረው፡፡

በየጊዜው ዓይነቱን የሚቀይረው የኮሮና ቫይረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ 260 መሊዮን ሰዎችን ያጠቃ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ሕይወት ነጥቋል፡፡ በኢትዮጵያ እስከ ትላንት ድረስ 6 ሺሕ 700 ሰዎች በቫይረሱ ሰበብ ሞተዋል፡፡  

 

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img