Monday, September 23, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ቢደርስ ፈጻሚዋ አሜሪካ መሆኗን የመንግሥት ባለሥልጣኑ ገለጹ


አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 15፣ 2014 ― የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አቶ ታዬ ደንደኣ፣ በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የሽብር ጥቃት ቢደርስ ፈጻሚው ‹‹ሆነ ብሎ ሐሰተኛ መረጃዎችን እያሠራጨ ነው›› ያሉት የአሜሪካ መንግስት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ በትላንትናው እለት ባወጣው መግለጫ፣ በአዲስ አበባ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የሽብር ጥቃት ሊኖር ይችላል ሲል በኢትዮጵያ ለሚኖሩ አሜሪካዊያን ዜጎች ማስጠንቀቂያ ሰዷል፡፡

አሸባሪዎች ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ የዲፕሎማቲክ ተቋማትን፣ የቱሪስት ቦታዎችን፣ የትራንስፖርትና ገበያ ማዕከላትን፣ በምዕራባዊያን ባለቤትነት የተያዙ ቢዝነሶችን፣ ሆቴሎችን፣ የመንግሥት ተቋማትን እና ሕዝብ የሚበዛባቸውን ቦታዎች ዒላማቸው ሊያደርጉ እንደሚችሉ ያስጠነቀቀው ኤምባሲው፣ አሜሪካዊያን እነዚህን ቦታዎች እንዳያዘወትሩና ለደኅንነታቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሯል።

እንደ አቶ ታዬ ደንደኣ ሁሉ ይህንኑ የአሜሪካ ኤምባሲን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዳንኤል ክብረት በትዊተር ገጻቸው አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡

ለአሜሪካን ኤምባሲ መግለጫ በተረት ምላሽ የሰጡት ዳንኤል፣ የጠላቱ ቤት ሲቃጠል በሕልሙ ያየው ሰው፣ ሕልሙ ውሸት ነው እንዳይባል ራሱ ቤቱን ማቃጠሉን አስታውሰው፣ የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫም እንደዚያ ይሆን ወይ ሲሉ ጥያቄ ሰንዝረዋል፡፡

በአዲስ አበባ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የሽብር ጥቃት ሊኖር ይችላል ሲል ያወጣው የአሜሪካ ኤምባሲ የሕወሓት ኃይሎች የአማራ ክልል ከተሞች የሆኑት ደሴ እና ኮምቦልቻን ተሻግረናል ማለታቸውን ተከትሎ ተደጋጋሚ አገሩን ለቃችሁ ውጡ የሚል የማስጠንቀቂያ መልእክቶችን ለዜጎቹ ሲያስተላልፍ ሰንብቷል፡፡

ነገር ግን መንግሥት አሜሪካን ጨምሮ ሌሎችም አገራት ያስለላለፉት ዜጎቻቸውን ውጡ የሚል ማሳሰቢያ የተጋነነ ነው ሲል አጣጥሎታል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img