Wednesday, November 27, 2024
spot_img

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ከተባበሰ ዜጎቿን ለማስወጣት በተጠንቀቅ ላይ እንደምትገኝ ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 14፣ 2014 ― አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ከተባበሰ የኢምባሲ ዲፕሎማቶቷን፣ ሠራተኞቹን እና አሜሪካዊያን ዜጎችን ከሀገሪቱ ለማስወጣት በጅቡቲ ልዩ ወታደሮቿን አዘጋጅታ እየተጠባበቀች መሆኑን ሲኤንኤን ዘግቧል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው የበድረ ገጹ እንደዘገበር ይህንኑ ከአገሪቱ ሲቪል እና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ተሰምቷል።

እነዚህ ምንጮች ገልፀዋል እንደተባለው ሁኔታው አስገዳጅ ከሆነ አሜሪካዊያንን ለማስወጣቱ ዕቅድ በመካከለኛው ምሥራቅ 3 የአሜሪካ ጦር መርከቦች በተጠንቀቅ ላይ ናቸው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ግን በአፍጋኒስታን እንደተደረገው በአሜሪካ ጦር ኃይል የታገዘ መጠነ ሰፊ የሆነ አሜሪካዊያንን የማስወጣት ዕቅድ ለጊዜው የለም ብሏል።

በቅርብ ጊዜያት በፌዴራል መንግስት እና በሕወሃት ኃይሎች መካከል የሚደረገው ጦርነት የተባባሰ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጦር ግንባር መከላከያን ለመምራት እንደሚዘምቱ ማሳወቃቸው አይዘነጋም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img