Saturday, September 21, 2024
spot_img

ሕብረት ኢንሹራንስ ሸሪዓ መር የሆነውን የተካፉል መድኅን አገልግሎት ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ኅዳር 13 2014 ሕብረት ኢንሹራንስ ኩባንያ እስላማዊ አስተምህሮን መርህ ያደረገው የተካፉል መድኅን (ኢንሹራንስ) ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሕብረት ኢንሹራንስ የሙስሊሙን ማኅበረሰብ አካታች የሆነ አገልግሎት መስጠትን ታላሚ አድርጎ እየሠራ መሆኑን የኢንሹራንሱ የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ዳይሬክተሩ ጥላሁን ታደሰን ጠቅሶ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስነብቧል፡፡

ይህንኑ የተካፉል አገልግሎት ለመጀመር በኩባንያው የአዋጭነት ጥናት እንደተከናወነ ስለመሆኑም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ይህ ተካፉል የተሰኘው ሸሪዓዊ መሠረት ያለው የመድኅን አገልግሎት፣ በኢትዮጵያ በቀዳሚነት የተጀመረው በግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ግሎባል ኢንሹራንስ በ2013 መስከረም ወር በጀመረው በዚህ አገልግሎት 1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ይንቀሳቀስበታል ተብሎ እንደሚገመት በተደረገው የኩባንያው የአዋጭነት ጥናት ተገልጧል፡፡

ከግሎባል በተጨማሪ አዋሽ ኢንሹራንስ በ10 ቅርንጫፎች አገልግሎቱን በማስጀመር የተከተለ ሲሆን፣ ኒያላ ኢንሹራንስ ከነዚህ ሁለት ኩባንያዎች ቀጥሎ እስላማዊ የመድኅን አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

በአሁኑ ወቅት በመስኮት ደረጃ የተካፉል መድኅን አገልግሎት ለመጀመር ከስምንት በላይ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እየጠበቁ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img