Wednesday, November 27, 2024
spot_img

ድሮንን ጨምሮ የመገናኛ መሳሪያዎች ያላቸው በ15 ቀናት እንዲያስመዘግቡ ትእዛዝ ተላለፈ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ኅዳር 10 2014 ― በመላ አገሪቱ የተለያዩ የኢንፎርሜሽን እና የመገናኛ መሳሪያዎች ያሏቸው ግለሰቦችና ተቋማት በ15 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘገቡ ትእዛዝ ያስተላለፈው የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ነው፡፡

ኢንሳ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገጹ ላይ ባስተላለፈው ትእዛዝ፣ ይህን ማድረግ ያስፈለገው በአገሪቱ ህልውና ላይ የሚያጋጥም አደጋን እንዲሁም ተደቅኖባታል ያለውን ‹‹የግዛት አንድነት ስጋት እና የሉአላዊነት ጥሰትን ለመከላከል ሁሉን አቀፍ የጥንቃቄ እርምጃዎች መውስድ አስፈላጊ በመሆኑ ነው›› ብሏል። አያይዞም እነዚህ የኮሚዩኒኬሽን መሳሪያዎች በአሸባሪዎች እና ግብረ-አበሮቻቸው ለሽብር አላማ እንዳይውሉ መሳሪያዎቹን እንደገና መመዝገብ እና በሚመለከተው አካል እጅ ስለመኖሩ ማወቅ ኤጀንሲው ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል ነው ያለው።

በዚህ መሠረት የጦር ሜዳ መነጽር፣ ኮምፓስ፣ የጂፒኤስ መሳሪያ፤ ወታደራዊ እና ሲቪል የመገናኛ መሳሪያዎች መገናኛ ሬዲዮ፣ ሳተላይት ስልክ፣ ቪሳት እና ቢጋን እንዲሁም ድሮኖች ያሏቸው ግለሰብ፣ መንግሥታዊና የግል ተቋማት፣ ኤምባሲዎች፣ ዲፕሎማቶች በአስራ አምስት ቀን ውስጥ እንዲያሳውቁ ጥሪ አቅርቧል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img