Wednesday, November 27, 2024
spot_img

በኦሮሚያ ክልል ከምሽት ሦስት ሰዐት በኋላ የሚደረግ የሰዎች እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጣለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 7፣ 2014 ― የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአገሪቱ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር በሚል በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ከምሽት ሦስት ሰዐት በኋላ የሚደረግ የሰዎች እንቅስቃሴ ላይ ገደብ መጣሉን አስታውቋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ግዛቸው ገቢሳን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ በክልሉ የሰዎች እንቅስቃሴ ላይ እስከ ምሽት 3 ሰዐት ብቻ የተፈቀደ ሲሆን፣ ተሽከርካሪዎች በአንጻሩ መንቀሳቀስ የሚችሉት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ብቻ ነው፡፡

ከሰዓት እላፊው በተጨማሪ በመንገድ ላይ ፍተሻዎች ይኖራሉ ያሉት ኃላፊው፣ በኬላዎች፣ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች እና ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ ፍተሻዎች እንደሚካሄዱ ጠቁመዋል፡፡

አቶ ግዛቸው ገቢሳ አብዛኛዎቹ ፍተሻዎች ምሽት ላይ የሚካሄዱ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ፍተሻዎቹ ዘላቂ ላይሆን ይችላሉ ብለዋል።

በሌላ በኩል የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊው በክልሉ የሚገኙ አከራዮች የተከራዮቻቸውን መታወቂያ በመያዝ በቀበሌና በአቅራቢያቸው በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እየሄዱ ማስመዝገብ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በትግራይ የተቀስቀሰው የሰሜን ጦርነት ወደ አጎራባች አማራ እና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ የሕወሓት ኃይሎች የደቡብ ወሎ ከተሞችን ይዘናል ካሉ በኋላ የፌደራሉ መንግሥት በመላ ኢትዮጵያ ተፈጻሚ የሚሆን ለስድስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ ማወጁ ይታወሳል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img