Sunday, September 22, 2024
spot_img

የትምህርት ሚኒስቴር ያለ እውቅናዬ ትምህርት አቋርጠዋል ላላቸው ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተሰማ

 

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 7 2014 የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ያለ እውቅናዬ ትምህርት አቋርጠዋል ላላቸው ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች በአንድ ሳምንት ውስጥ ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምሩ ማስጠንቂያ መስጠቱ ተሰምቷል፡፡

ትምህርት አቋርጠዋል የተባሉት ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች፣ ለተማሪ ወላጆች በላኩት ደብዳቤ የፀጥታ ስጋትን በምክንያትነት መጥቀሳቸውን የካፒታል ጋዜጣ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ትምህርት ቤቶቹ ደብዳቤውን ለወላጆች መላካቸውን ተከትሎ የትምህርት ሚኒስቴር፣ ከሚመለከተው የመንግስት አካል አቅጣጫ ሳይሰጥ ደብዳቤውን ለወላጆች መላክ አግባብ አለመሆኑን በመጥቀስ፣ ትምህርት ቤቶችን ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ማሳሰቡም በዘገባው ሠፍሯል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ያለ እውቅናዬ ትምህርት አቋርጠዋል ያላቸው ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች በአንድ ሳምንት ውስጥ ትምህርት የማይቀጥሉ ከሆነ ፍቃድ ሊሰርዝ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ 26 ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል 24 ትምህርት ቤቶች በአዲስ አበባ ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ የሚገኙ ናቸው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img