Monday, November 25, 2024
spot_img

በትግራይ ጦርነቱ ከጀመረ አንስቶ 47 የኩላሊት ታማሚዎች በዲያሌሲስ ቁሳቁስ እጥረት ሰበብ መሞታቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ ማስተባበሪያ ቢሮ ሪፖርት አመለከተ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ኅዳር 6 2014 ― በትግራይ ክልል ከተጀመረ አንድ ዓመት በተሻገረው ጦርነት 47 የኩላሊት ታማሚዎች በዲያሌሲስ ቁሳቁስ እጥረት ሰበብ መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) የአይደር ሆስፒታል ሪፖርት ጠቅሶ ይፋ አድርጓል፡፡

እንደ ቢሮው ከሆነ ከሞቱት ውጪ የመድሃኒት አቅርቦት እጥረት በመኖሩ ምክንያት በአሁኑ ወቅት ሌሎች 32 የጠና የኩላሊት ሕመም ያለባቸው ሰዎች፣ በሳምንት ለሦስት ጊዜያት ሕክምና ማግኘት ሲኖርባቸው ለሁለት ጊዜያት ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

በተመሳሳይ የካንሰር ታማሚዎችም የቁሳቁስ እጥረቱ ተጠቂ መሆናቸውን ያመለከተው ኦቻ፣ በተለይ አዳዲስ የካንሰር ታማሚዎች መድሃኒት ማግኘት እንዳልቻሉ አመልክቷል፡፡ የኦቻ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ወደ አምስት መቶ ገደማ የካንሰር ታማሚዎች ሕክምና ማግኘት አልቻሉም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img