Friday, October 18, 2024
spot_img

ጅቡቲ በጎረቤቶቿ ላይ ለሚፈጸም ጣልቃ ገብነት መጠቀሚያ እንደማትሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ኅዳር 6 2014 ― የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ አገራቸው በጎረቤት አገር ላይ ለሚፈጸም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት መጠቀሚያ ሆና እንደማታገለግል ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት በጂቡቲ የአሜሪካ ጦር አዛዥ የሆኑት ሜጀር ጄነራል ዊሊያም ዛና፣ በኢትዮጵያን ቀውስ የሚከሰት ከሆነ የአሜሪካ ወታደሮች በኢትዮጵያ የሚገኙ የኤምባሲ ሠራተኞችን፣ አሜሪካውያንን እና የሌሎች አገራት ዜጎችን ከኢትዮጵያ ለማስወጣት እና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝርዝር የሆነ ዕቅድ ማውጣታቸውን እና ዝግጅት ማድረጋቸውን ለመገናኛ ብዙኃን ከተናገሩ በኋላ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት የጂቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በትዊተር ገጻቸው ላይ አንዳንዶች የጂቡቲ ግዛት በጎረቤት አገራት ላይ ለሚፈጸም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን እንደሚገልጹ አመልክተው፣ ሆኖም ግን ‹‹ከጎረቤቶቹ ጋር ትስስር ያለው የጂቡቲ መንግሥት ይህ እንዲሆን አይፈቅድም›› ብለዋል፡፡

በጂቡቲ የአሜሪካ ጦር አዛዥ የሆኑት ሜጀር ጄነራል ዊሊያም ዛና የኢትዮጵያ አለመረጋጋት ለቀጠናው ስጋት እንደሚሆን የተናሩት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡  

ኢትዮጵያ አብዛኛው ከውጭ የሚገቡ እና የሚወጡ አብዛኛው ምርቶችን ለማጓጓዝ የጂቡቲ ወደብ እንደምትጠቀም ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img