Wednesday, November 27, 2024
spot_img

ሳፋሪኮም ከኢትዮ ቴሌኮም መሠረተ ልማት ለመከራየት ድርድር ላይ እንደሚገኝ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ ኅዳር 5፣ 2014 ― በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ ሥራ እንደሚጀምር የገለጸው ሳፋሪኮም፣ ከኢትዮ ቴሌኮም መሠረት ልማት ለመከራየት ድርድር ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።

ይህንኑ ሪፖርተር ጋዜጣ ሥማቸውን ካልጠቀሳቸው ኃላፊ መስማቱን ዘግቧል።

በያዝነው ዓመት ከመሠረተ ልማት ገቢ እናገኛለን ብለን አቅደን ነበር” ያሉት ኃላፊው፣ ነገር ግን የውጭ አዳዲስ ኦፕሬተሮች ወደ ሥራ የሚገቡበት ጊዜ አልታወቀም፡፡ የራሳችን የኪራይ ዋጋም በትክክል አልታወቀም፡፡ የራሳችን የኪራይ ዋጋ አቅርበንላቸው አሁን በድርድር ላይ ነን ማለታቸው ተመላክቷል።

ከኢትዮ ቴሌኮም መሠረተ ልማት ለመከራየት ድርድር ላይ ነው የተባለው ሳፋሪኮም፣ ከሰሞኑ በፀጥታ ስጋት ሠራተኞቹን ከኢትዮጵያ ማስወጣቱ መነገሩ አይዘነጋም።

በሌላ በኩል ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 የመጀመርያ ሦስት ወራት ውስጥ 1.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማጣቱን ገልጿል።

በዚህም ምክንያት የ2014 የመጀመርያ ሩብ ዓመት ዕቅዱ ከ15.4 ቢሊዮን ገቢ በ12 ከመቶ መውረዱ ተነግሯል።

ድርጅቱ የሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርቱን ለገንዘብ ሚኒስቴርና ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ኤጀንሲ በሒልተን ሆቴል ያቀረበ ሲሆን፣ አጠቃላይ ትርፉ 5.9 ቢሊዮን ብር ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህም ለሩብ ዓመቱ ካቀደው 4.8 ቢሊዮን ብር በ1.1  ቢሊዮን ብር  በልጧል፡፡

ተቋሙ አገልግሎቱ በሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ፣ ሙሉ ትግራይና ከፊል አፋር ውስጥ ተቋርጧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img