አምባ ዲጂታል፣ረቡዕ ኅዳር 1፣ 2014 ― በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ትልቁ የንግድ ማእከል መርካቶ አካበቢ በሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ የአስቸኳይ አዋጁን ተከትሎ ከሕግ አግባብ ውጪ ፍተሻ እና ማዋከብ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተሰምቷል፡፡
በሥፍራው በሚገኙ አንዳንድ የንግድ ሱቆች፣ ከሕግ አግባብ ውጪ በፍተሸ ሰበብ ብር አከማችኋል በሚል መዋከብ እየተፈጸመባቸው መሆኑን አምባ ዲጂታል ከአንዳንድ ቅሬታ አቅራቢዎች ሰምቷል፡፡
ይኸው ድርጊት መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይፋ ካደረገበት ከጥቅምት 23፣ 2014 ማግስት አንስቶ በንግድ ሥፍራው እንደሚፈጸም ቅሬታ አቅራዎቹ ተናግረዋል፡፡ ይህ ድርጊት በመርካቶ አካባቢ አዋጁን ተገን አድርገው ሕገ ወጥ ድርጊት ለሚፈጽሙ ከለላ መስጠቱንም አያይዘው ገልጸዋል፡፡
እነዚህ የንግድ ማህበረሰብ አባላት የሚመለከተው የመንግስት አካል ቁጥጥር እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ በመላ አገሪቱ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለቀጣይ ስድስት ወራት የሚቆይ ነው፡፡