Sunday, November 24, 2024
spot_img

የመንግሥታቱ ድርጅት የከባድ መኪኖች አሸከርካሪዎች የሆኑ ከ70 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ረቡዕ ኅዳር 1 2014 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 72 የዓለም ምግብ ፕሮግራም የከባድ መኪና አሸከርካሪዎች አፋር ክልል ሰመራ ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሬውተርስ እና እና አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግበዋል፡፡

ሬውተርስ የድርጅቱ ቃል አቀባይ በዓለም ምግብ ድርጅት ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ 72 አሸከርካሪዎች ሰመራ ከተማ ላይ መታሰራቸውን አረጋግጠውልኛል ያለ ሲሆን፣ ‹‹ሠራተኞቹ ለምን እንደታሰሩ ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተነጋገርን ነው›› እንዳሉት አስነብቧል፡፡

በተመሳሳይ በትላንትናው እለት ኢትዮጵያውያን የሆኑ ቢያንስ 16 የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው መነገሩ አይዘነጋም፡፡

በትላናትናው እለት አመሻሹ ላይ የወጣውን ይህን ዜና ተከትሎ የአሜሪካ መንግሥት ተፈጸመ የተባለው የዓለም አቀፍ ድርጅቱ ሠራተኞች እስር አሳስቦኛል ብሏል፡፡ መንግስት ሠራተኞቹ ለምን እንደታሰሩ ያለው ነገር ባይኖርም፣ አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግየት ብሎ ባወጣው ዘገባ ስድስቱ መለቀቃቸውን አስነብቧል፡፡  

የመንግሥታቱ ድርጅት ታሰሩብኝ ስላላቸው ሠራተኞቹ ጉዳዩ የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን የሰጠው ማብራሪያ የለም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img