Tuesday, November 26, 2024
spot_img

የአፍሪካ ኅብረት ሠራተኞቹን በጊዜያዊነት ከአዲስ አበባ ወደ ሌላ ቦታ ሊያዘዋውር ነው በሚል ሐሰተኛ መረጃ ተሠራጭቶብኛል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጥቅምት 29፣ 2014 ― የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሠራተኞቹን በጊዜያዊነት ከአዲስ አበባ ወደ ሌላ ቦታ ሊያዘዋውር ነው በሚል ሐሰተኛ መረጃ እንደተሠራጨብኝ እወቁት ብሏል፡፡  

ኮሚሽኑ በድረ ገጹ እንዳስታወቀው፣ የኮሚሽኑ ሠራተኞች በጊዜያዊነት ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ በሊቀመንበሩ ጥሪ ቀርቧል በሚል መረጃ መሠራጨቱን ነው የገለጸው፡፡

ኮሚሽኑ ይኸው መረጃ በሊቀመንበሩ በውስጥ ተላልፏል በሚል ተመሳስሎ እንደተሰራጨም ነው ያመለከተው፡፡

በመሆኑም የተሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ እና መሠረት የሌላው መሆኑን እወቁት ሲሉ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ሙሳ መሕመት ፋቂ ቃል አቀባይ ኤባ ካሎንዶ አስታውቀዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ዋና መቀመጫው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img