አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ጥቅምት 26፣ 2014 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በመላ አገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ በመታወጁ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ሰሌዳን እና ዝግጅት ማቋረጡን በዛሬው እለት አስታውቋል፡፡
6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች አከናውኖ ማጠናቀቁን ያስታወቀው ቦርዱ፣ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ደግሞ በታኅሣሥ ወር ምርጫውን ለማከናወን የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ተግባራትን ማከናወን ጀምሮ እንደነበር አመልክቷል፡፡
ነገር ግን የኢ.ፌዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀውን አገር አቀፍ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በትላንትናው እለት ጥቅምት 25፣ 2014 ማጽደቁን ተከትሎ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ሰሌዳን እና ዝግጅትን ያቋረጠ መሆኑን እወቁልኝ ብሏል፡፡
ምርጫ ቦርድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በሚገኙ በአብዛኛው የክልል ምክር ቤትን በያዙ 17 ምርጫ ክልሎች ምርጫ ለማካሄድ ጊዜያዊ ሌዳ ይዞ የነበረው ለታኅሣሥ 21፣ 2014 ነበር፡፡