Tuesday, November 26, 2024
spot_img

መንግስት እንደ ሬውተርስ ያሉ ዓለም አቀፍ ዜና ወኪሎች ሐሰተኛ መረጃ እያሠራጩ ነው አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ጥቅምት 25፣ 2014 ― መንግስት እንደ ሬውተርስ ያሉ ዓለም አቀፍ ዜና ወኪሎች የሕወሓት ኃይሎች ያልተቆጣጠሯቸውን አከባቢዎች እንደተቆጣጠረ በማስመሰል ሐሰተኛ መረጃ እያሠራጩ ነው በማለት ከስሷል።

ይህንኑ በዛሬው እለት የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫው አስታውቋል።

አገልግሎቱ የሕልውና ጦርነት ላይ ነን ባለበት መግለጫው፣ ግጭት ለማባባስ ይሠራል ያለው ፌስቡክ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጽሑፍ ማንሳቱን አውግዟል።

ፌስቡክ መልዕክቱን በመሰረዝ ከሕዝባዊ ሕወሓት ጋር ማበሩን እንዳስመሰከረም አገልግሎቱ ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሦስት ቀናት በፊት ባሰፈሩት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ሕዝብ ‘የክት’ ጉዳዩን አቆይቶ ሕወሓትን ‘ለመመከት፣ ለመቀልበስና ለመቅበር ማናቸውንም መሳሪያ እና አቅም ይዞ በሕጋዊ አደረጃጀት’ ዘመቻውን እንዲቀላቀል በማለት ጥሪ አቅርበው ነበር።

ሆኖም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሑፍ የኩባንያውን ደንቦች ጥሷል ያለው ፌስቡክ ጽሑፉን መሰረዙ መነገሩ ይታወቃል።

በፌዴራል መንግስት እና በሕወሓት መካከል እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት ከሰሞኑ ተባብሶ መቀጠሉ እየተነገረ ይገኛል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img