Sunday, September 22, 2024
spot_img

ፌስቡክ ከሁለት ቀናት በፊት የተለጠፈውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፖስት አነሳ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጥቅምት 24፣ 2014 ― ግዙፉ የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ፌስቡክ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ አካውንት ከሁለት ቀናት በፊት የተለጠፈውን ‘ፖስት’ አንስቷል።

በዕለቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሰፈሩት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ሕዝብ ‘የክት’ ጉዳዩን አቆይቶ ሕወሓትን ‘ለመመከት፣ ለመቀልበስና ለመቅበር ማናቸውንም መሳሪያ እና አቅም ይዞ በሕጋዊ አደረጃጀት’ ዘመቻውን እንዲቀላቀል በማለት ጥሪ አቅርበው ነበር።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ የመጣው የሕወሓት ኃይሎች የደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞችን ተቆጣጥረናል ማለታቸውን ተከትሎ ነበር።

ቢቢሲ የፌስቡክ ቃል አቀባይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፖስት የኩባንያውን ደንቦች በመጣሱ ማንሳታቸውን እንደነገሩት ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ ፌስቡክ በዕለቱ የተለጠፈውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፖስት ጠብ ጫሪ ነው ብሎ ነው ያነሳው።

ፌስቡክ ኩባንያ ከዚሁ ጋር በተገናኘ በቅርቡ ከቀድሞ ሠራተኛው ኢትዮጵያን ጨምሮ በአንዳንድ ሀገራት የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን መግታት እየቻለ አላስቆመም የሚል ውንጀላ እንደቀረበበት አይዘነጋም፡፡ ይህንኑ ለሁለት ዓመታት ያህል በኩባንያው የሠሩት የዳታ ሳይንቲስቷ ፍራንሴስ ሃውገን በአሜሪካ ሕግ አውጭ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ተናግረዋል።

አሁን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ፖስት ያነሳው ኩባንያው፣ ከዚሁ ጋር በተገናኘ በቅርቡ ከቀድሞ ሠራተኛው ኢትዮጵያን ጨምሮ በአንዳንድ ሀገራት የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን መግታት እየቻለ አላስቆመም የሚል ውንጀላ እንደቀረበበት አይዘነጋም፡፡ ይህንኑ ለሁለት ዓመታት ያህል በኩባንያው የሠሩት የዳታ ሳይንቲስቷ ፍራንሴስ ሃውገን በአሜሪካ ሕግ አውጭ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ፌስቡክ በአማራ ክልል እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት ‹‹ፋኖ›› ከተሰኘው ታጣቂ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉና ሁከት አባባሽ ጥሪዎች ሲያዛምቱ በነበሩ አካውንቶች ላይ መረጃ እያለው እርምጃ አልወሰደም በሚል ወቀሳ ተሰንዝሮበት ነበር።

በሌላ በኩል ፌስቡክ ከጥቂት ሳምንት በፊት ይፋ በተደረገበት ምስጢራዊ የተባለው የጥቁር መዝገብ ሰነድ ላይ በመንግስት ሸኔ የሚባለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር የሚለውን ቡድን መንግሥታዊ ያልሆኑ ሁከት ፈጣሪ አካላት (ቫዮለንት ነን ስቴት አክተርስ) በሚለው ዝርዝር ውስጥ አካቶታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img