Friday, November 22, 2024
spot_img

የአሜሪካ መንግስት የኢትዮጵያን የአጎዋ ተጠቃሚነት ዕድል አነሳ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጥቅምት 23፣ 2014 ― የአሜሪካው መንግስት የኢትዮጵያን የአጎዋ ተጠቃሚነት ዕድል ማንሳቱን አስታውቋል።

አገሪቱ የኢትዮጵያን የአጎዋ ተጠቃሚነት ዕድል ያነሳችው በአገሪቱ ተፈጽመዋል የሰብአዊ ጥሰቶችን በመጥቀስ ነው።

የአሜሪካ መንግስት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የማሊ እና የጊኒን የአጎዋ ዕድል ተጠቃሚነት አንስቷል።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብቻ ኢትዮጵያ 237 ሚሊዮን ዶላር ምርት አጎዋን በመጠቀም ያለ ቀረጥ ወደ አሜሪካ ልካለች፡፡ ነገር ግን አሜሪካ መንግሥት የትግራዩን ሰብዓዊ ቀውስ አልፈታም በሚል ዕድሉን ከኢትዮጵያ ላይ እነጥቃለሁ ሲል እየዛተ መቆየቱ ይታወቃል።

በተመሳሳይ ይህንኑ ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በፊት የተሰጣትን ከታሪፍና ከኮታ ነፃ የሚያደርገውን ‹‹አፍሪካን ግሮውዝ ኤንድ ኦፖርቹኒቲ አክት›› (አጎዋ) ተጠቃሚነት እንድታጣ ለሕወሃት በሎቢ አድራጊነት የሚሠራው ቮን ባተን ሞንቲግዩ የተባለ ድርጅት ሲወተውት ቆይቷል።

በተለይም ኢትዮጵያ ከአጎዋ መሰረዟ አገር ውስጥ የሚገኙት እንደ ካልቪን ክለይን፣ ቶሚ ሂልፊገር እና ኤችኤንድኤምን የመሳሰሉ በዓለም ታዋቂ አምራቾች መቆየታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ስለመሆኑም ቀድመው ስጋታቸውን የሚያጋሩ ነበሩ።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img