Tuesday, November 26, 2024
spot_img

መንግሥት ከሕወሓት ጋር የንግግር ዕድል ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጠ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጥቅምት 22፣ 2014 ― የፌዴራል መንግስት ጦርነት ውስጥ ከሚገኘው ሕወሓት ጋር የንግግር ዕድል ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ቢልለኔ ሥዩምን ጠቅሶ ኤንፒአር እንደዘገበው፣ መንግስት ከሕወሓት ጋር ለመነጋገር እድል ሊሰጥ ይችላል።

አንድ ዓመት ሊደፍን ሁለት ቀናት የቀሩት በፌዴራል መንግስት እና በሕወሃት ኃይሎች መካከል ያለው ጦርነት የሔወሃት ኃይሎች የአማራ ክልል ከተሞች የሆኑትን ደሴን እና ኮምቦልቻን ተቆጣጥረናል ማለታቸው መነገሩ ይታወሳል።

እነዚህ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ሕዝቡ የክት ጉዳዩን አቆይቶ ሕወሓትን ‹ለመመከት፣ ለመቀልበስና ለመቅበር ማናቸውንም መሳሪያ እና አቅም ይዞ በሕጋዊ አደረጃጀት መዝመት አለበት›› ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹የመረረውን ትግል ታግለን፣ ጣፋጩን ድል እናጣጥማለን›› ባሉበት መግለጫ፣ ‹‹ሕወሓት በአራት ግንባሮች ተኩስ ከፍቶ አገር የማፍረስ ተግባሩን ገፍቶበታል›› ያሉ ሲሆን፣ ‹‹ሰሞኑን ያለ የሌለ ኃይሉን ወደ ወሎ ግንባር አምጥቷል። አገር ለማጥፋት የመጣ መንጋ አገር ለማዳን የተነሣን ኃይል ይረብሸው ይሆናል፣ ሊያሸንፈው ግን አይችልም›› ሲሉም ገልፀው ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img