Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ከደሴ እና አቅራቢያው ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ የነበሩ ተፈናቃዮች ከሸኖ ከተማ ማለፍ አትችሉም መባላቸው ተነገረ

 

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጥቅምት 22፣ 2014 ― በደሴ እና አቅራቢያው ባለው ጦርነት ሰበብ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ የነበሩ የተፈናቀሉ ሰዎች ከሸኖ ከተማ ማለፍ አትችሉም መባሉ ተነግሯል፡፡

እነዚህን የተፈናቀሉ ሰዎች የጫኑ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተሸከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ ማለፍ አትችሉም ተብለው በሸኖ ከተማ እንግልት እንደደረሰባቸው የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

ባለፉት ሦስት ሳምንታት አገርሽቶ በስፋት እየተካሄደ የሚገኘው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጦርነት በደሴ እና ኮምቦልቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ ይነገራል፡፡ እነዚህ ሁለት ከተሞች የሕወሓት ኃይሎች ወደ ሰሜን ወሎ አካባቢዎች መግፋቱን ተከትሎ በበርካታ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አስጠልለው ቆይተዋል፡፡

 

ውጊያው በሁለቱ ከተሞች በስፋት እየተካሄደ መሆኑን ተከትሎ ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ ለመሸሽ ቢሞክሩም፣ ሸኖ ከተማ ላይ ማለፍ አልቻሉም የተባሉትን ሰዎች በተመለከተ በመንግስት ባለስልጣናት በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img