Saturday, September 21, 2024
spot_img

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ አራት ቦታዎች ላይ የአደባባይ የዋይፋይ አገልግሎት ሊያቀርብ በሙከራ ላይ መሆኑ ተሰማ

 

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጥቅምት 22፣ 2014 ― ኢትዮ ቴሌኮም እንጦጦ ፓርክን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አራት ዋና ዋና ቦታዎች ላይ የአደባባይ የዋይፋይ አገልግሎት ሊያቀርብ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

 

ካፒታል ጋዜጣ ይዞት በወጣው ዘገባ እንዳመለከተው፣ ኩባንያው በቅርቡ አገልግሎቱን የሚጀምርባቸው ቦታዎች እንጦጦ ፓርክን ጨምሮ መስቀል አደባባይ፣ የወዳጅነት አደባባይ እና አንድነት ፓርክ ናቸው፡፡

 

ኢትዮ ቴሌኮም በነዚህ ቦታዎች ላይ በሚሰጠው አገልግሎት ደንበኞች በአነስተኛ ዋጋ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ነው ዘገባው ምንጮቼ ነግረውኛል ብሎ ያመለከተው፡፡ በዚሁ መሠረት በአደባባዮቹ እና ፓርኮቹ ለአንድ ሰአት አግልግሎቱን የሚጠቀም ሰው 5 ብር የሚከፍል ሲሆን፣ ለሁለት ሰአት 8 ብር እንዲሁም ለ3 ሰአት ደግሞ 12 ብር እንዲከፍል ይደርጋል፡፡ ደንበኞች ለአገልግሎት የሚከፍሉት ገንዘብ ከስልካቸው ላይ ይቆረጣል ተብሏል፡፡

 

ኢትዮ ቴሌኮም ይህንኑ አገልግሎት ለመስጠት ሙከራውን መጀመሩ የተጠቀሰ ሲሆን፣ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ አገልግሎቱን መስጠት እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡

 

በኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜ ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ የነበረው ኢትዮ ቴሌኮም፣ የተለያዩ ማስፋፊያዎችን እያደረገ እንደሚገኝ በኃላፊዎቹ በኩል ይናገራል፡፡ ኩባንያው በአገሪቱ በአጠቀላይ ከ50 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉትም ገልጧል፡፡

በኢትዮጵያ ከኢትዮ ቴሌኮም በተጨማሪ ባለፈው ዓመት መንግስት ባወጣው ጨረታ አሸናፊ የሆነው የኬንያው ሳፋሪኮም የሚመራው ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ በቀጣይ ወራት አገልገሎት መስጠት እንደሚጀምር ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ሳፋሪኮም ካሸነፈው አንድ ቦታ ተጨማሪ ሌላ ጨረታ ያወጣ ሲሆን፣ የዚሁ ሁለተኛውን የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ ለመስጠት የወጣው ጨረታ ውጤት አሸናፊው በመጪው ጥር ወር ይፋ እንደሚያደርግ ተነግሯል።

የሁለተኛው ዙር ጨረታ በድጋሚ የወጣው በመጀመሪያው ዙር ከሳፋሪኮም በመቀጠል ሁለተኛ የወጣው በቻይና የሲልክ ሮድ ፈንድ ድጋፍ ተደርጎለት 600 ሚሊዮን ዶላር ያቀረበው ኤምቲኤን አነስተኛ መጫረቻ በማቅረቡ ሳያሸንፍ በመቅረቱ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img