Monday, November 25, 2024
spot_img

የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኢራን የምታመርታቸው ድሮኖች በትግራይ ጦርነት ጥቅም ላይ ውለዋል አለ

 

 

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ጥቅምት 20፣ 2014 ― የአሜሪካው ግምጃ ቤት ኢራን የምታመርታቸው ድሮኖች በትግራይ ጦርነት ጥቅም ላይ ውለዋል ያለው ለወታደራዊ ዓላማ ከሚውሉ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ መጣሉን ባሳወቀበት መግለጫው ነው፡፡  

 

ግምጃ ቤቱ ባወጣው መግለጫ በትግራዩ ጦርነት ጥቅም ላይ ውለዋል ያላቸው ለወታደራዊ ዓላማ የሚውሉ ሰው አልባ ድሮኖች የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ኃይል ያመረታቸው መሆኑን አመልክቷል፡፡

 

የአሜሪካ መንግስት ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸው አራት የኢራን ባለስልጣናት እና ሁለት የንግድ ተቋማት ላይ ማእቀቡ መጣሉንም አስታውቋል፡፡  

 

የአሜሪካ ግምጃ ቤት በዚሁ መግለጫው ከድሮኑ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ማዕቀብ ከተጣለባቸው ኢራናዊያን ባለሥልጣናትና ድርጅቶች ጋር የንግድ ግንኙነት የሚያደርጉ አካላትን፣ በአሜሪካ ያላቸውን ገንዘብ ወይም ንብረት እንደሚያግድና የአሜሪካን የፋይናንስ ሥርዓት እንዳይጠቀሙ እንደሚያደርግ አስጠንቅቋል።

 

የግምጃ ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ዋሊ አዴዬሞ እንዳሉት ኢራን እና አጋሮቿ ለወታደራዊ ዓላማ በሚውሉ ሰው አልባ ድሮኖች የአሜሪካ ኃይሎችን እና አጋሮቿን አጥቅተዋል ብለዋል፡፡

 

የባይደን አስተዳደር የጣለውን ማእቀብ በተመለከተ ኢራን መልስ አልሰጠችም፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ ሥሟ የተጠቀሰው የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትም ያሉት ነገር የለም፡፡  

 

በሚቀጥለው ሳምንት አንድ ዓመት በሚደፍነው በትግራይ ክልል ጀምሮ አሁን በአማራ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጦርነት በተለይ በፌዴራል መንግስት በኩል ድሮኖች ጥቅም ላይ መዋላቸው በሕወሃት ሰዎች መነገሩ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img