Sunday, September 22, 2024
spot_img

የአሜሪካ የልማት ባንክ በትግራይ ጦርነት ሰበብ ለነ ሳፋሪኮም ይሰጣል የተባለውን 500 ሚሊዮን ዶላር ማዘግየቱ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ጥቅምት 18፣ 2014 ― የአሜሪካው የልማት ባንክ ዓለም አቀፍ የልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን በመጪው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ ሥራ እጀምራለሁ ላለው በሳፋሪኮም ለሚመራው ጥምረት ይሰጣል ተብሎ የነበረውን 500 ሚሊዮን ዶላር ማዘግየቱ ተነግሯል፡፡

የልማት ባንኩ ከዚህ ቀደም በሳፋሪኮም የሚመራው ጥምረት በኢትዮጵያ ጨረታ ተሳትፎ ካሸነፈ ለንድፍ፣ ግንባታ እና ስራ ማስኬጃ ይውላል የተባለውን 500 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለመስጠት ተስማማቶ እንደነበር ይፋ ተደርጎ ነበር፡፡

ሆኖም አሜሪካ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተገናኘ ባሉ ሁኔታዎች ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ክልከላ መጣሏ እና በቅርቡም በፕሬዝዳንትዋ ጆ ባይደን በኩል ለተጨማሪ ማእቀብ ትእዛዝ መፈረሟ ይታወቃል፡፡

የኬንያው ቢዝነስ ዴይሊ ይዞት በወጣው ዘገባ እንዳመለከተው የልማት ባንኩ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተገናኘ ሁኔታዎችን በቅርበት እየመረመርኩ ነው ያለ ሲሆን፣ በዚሁ ሰበብ የሚሰጠውን ገንዘብ አዘግይቷል፡፡

የልማት ባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ በትግራይ ጦርነት የታጠቁ ኃይሎች በንጹሐን ላይ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸውን ገለጸው፣ አገራቸው ለጉዳዩ ምላሽ ለመስጠት ቁርጠኛ አቋም መያዟን መግለጻቸውም በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ብሊንክን ከዚህ ቀደም አገራቸው በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ ከጣለችው የቪዛ ክልከላ በተጨማሪ ለኢትዮጵያ መንግስት በምትሰጠው የኢኮኖሚ እና የጸጥታ ዕርዳታ ላይ ገደብ እንደተጣለም አስታውቀው ነበር፡፡ ይኸው ውሳኔ በኢትዮጵያ ለቴሌኮም አቅርቦት ላሸነፈው ለሳፋሪኮም በሚሰጠው የብድር ሒደት ላይ እንቅፋት እንዳይፈጥር ተሰግቶ ነበር።

መንግስት ለሁለት የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ፈቃድ ለመስጠት ጨረታ ያወጣው ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ጨረታውን ካሸነፈው ሳፋሪኮም ጋር የደቡብ አፍሪካው ቮዳኮም እና የብሪታንያው ቮዳፎን አብረውት ይገኛሉ፡፡

አዲሱ የቴሌኮም አቅራቢ በኢትዮጵያ ሥራውን ለመጀመር እየተሰናዳ መሆኑን በቅርቡ ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img