Monday, November 25, 2024
spot_img

አሜሪካ በትግራይ ክልል አዲስ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ግጭት የሚባባብስ ነው አለች

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጥቅምት 10፣ 2014 ― አሜሪካ በትግራይ ክልል መቀመጫ መቐለ ከተማ አዲስ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ግጭት የሚባባብስ ነው ስትል ተቃውማዋለች።

የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቃባይ ኔድ ፕራይስ በትዊተር ባሰፈሩት መልዕክት «በመቀሌ እና አካባቢው ስለተፈጸሙት ጥቃቶች ተዓማኒነት ያላቸው ዘገባዎች አይተናል። አሁንም ሰላማዊ ሰዎችን ለጉዳት እየዳረገ የሚገኘው ግጭት መባባሱን ዩናይትድ ስቴትስ ትቃወማለች » ብለዋል።

ፕራይስ «የኢትዮጵያ መንግስት እና ሕወሃት ውጊያውን አቁመው ውይይት መጀመር አለባቸው” በማለት አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ አጋር የሆነችው አሜሪካ ትግራይ ውስጥ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ግንኙነቷ እየሻከረ መጥቷል።

በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ወደ አፋር እና የአማራ ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት እንዲቆም በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና ለማሳደር የማዕቀብ እርምጃዎችን ለመውሰድ አማራጮችን እንደምታጤን አገሪቱ ማስታወቋም አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የዩናይትድድ ስቴትስ መንግስት ጫና ለማሳደር የተከተለው መንገድ «እውነታውን ያላገናዘበ» በማለት በበኩሉ እንደማይቀበለው ገልጿል።

ከሰሞኑ በቀጠለው ውጊያ በትግራይ ክልል መቀመጫ መቐለ ከተማ በተያዘው ሳምንት ለሁለት ጊዜያት የአየር ጥቃት እንደተፈፀመና የሰዎች ሕይወት መቀጠፉንም መረጃዎች አመልክተዋል።

ከፌዴራል መንግስት ጋር ውጊያ ውስጥ የሚገኘው ሕወሃትም በአማራ ክልል እና በአፋር ከባድ መሳሪያ ተኩሶ ንጹሐንን መግደሉ ሲነገር ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img