አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጥቅምት 8፣ 2014 ― ወደ ትግራይ ክልል መቀመጫ መቐለ ከተማ የአውሮፕላን ጥቃት መሰንዘሩን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ የረድኤት ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
የዜና ወኪሉ የአውሮፕላም ጥቃቱ ኢላማ ያደረገው ምን እንደሆነ እና በጥቃቱ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የጠቀሰው ነገር ባይኖርም፣ ሌሎች ምንጮች ጥቃቱን የሰነዘረው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ኃይል መሆኑንና በጥቃቱም መሰቦ አካባቢ የሚገኘውን የሕወሃትን የትጥቅ እና ስንቅ መጋዝን ማውደሙን አመልክተዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ከአገር መከላከያ ሠራዊትም ሆነ ከሕወሃት በኩል ይህ ዘገባ እስከተሰናዳበት ሰአት ድረስ የተሰጠ ይፋዊ ማብራያ የለም፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረገው ጦርነት ከባለፈው ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ እንዳገረሸ መነገሩ አይዘነጋም፡፡