Saturday, November 23, 2024
spot_img

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ያላቸውን ከ100 በላይ አመራሮች በሕግ እንዲጠየቁ በማድረግ ላይ እገኛለሁ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ጥቅምት 6፣ 2014 ― የከተማው አስተዳደሩ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ያላቸው 120 አመራሮች እና ባለሞያዎች በመሬት ማኔጅመንት ቢሮ ውስጥ ከሚገኙ ጀምሮ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ድረስ በቀጥታ በብልሹ አሰራር ውስጥ የተሳተፉ መሆናቸውን አሳውቋል፡፡

ይህንኑ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጥራቱ በየነ በከተማዋ በተፈጸመ ሕገ ወጥ የመሬት ወረራ እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመቆጣጠር እየተወሰደ ባለው እርምጃ ዙሪያ ለመገኛኛ ብዙሃን በገለጹበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው የከተማ አስተዳደሩ 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ እና ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ሽፋን ህገ ወጥ የመሬት ወረራ እንዳይስፋፋ አስቀድሞ ዝግጅት ተደርጎ መሰራቱን ገልጧል፡፡ ከለውጡ በፊት በነበረው ብልሹ የአሰራሮች ምክንያት የመሬት እና በመሬት ነክ ጉዳዮች ላይ ስር የሰደደ ውስብስብ ችግር መኖሩን የገለጹት አቶ ጥራቱ፣ ከለውጡ ወዲህም በመሬት ዘርፍ የአደረጃጀት፣ የአሰራር ማሻሻያ ስራዎች መሠረታቸውን ጠቅሰው በተለይ የአርሶ አደሩን የአርሶ አደር ልጆችን በመሬታቸው ተጠቃሚ እንዲሆን አሰራሮች ተዘርግተው፣ መመሪያዎችም ጸድቀው ስራ ላይ እንዲውሉ መደረጋቸውን አመልክተዋል፡፡

ነገር ግን አንዳንድ ቡድኖችና ደላሎች በከተማዋ በተለይ በማስፋፊያ አካባቢዎች ሕገ ወጥ የመሬት ወረራዎችን የማካሄድ ሙከራዎችና ተግባራት እየተደረገ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ስራ አስኪያጁ፣ በቅርቡም ካርታ ከወጣላቸው 2 ሺሕ 170 ይዞታዎች ውስጥ በተደረገ ማጣራት 497 ቦታዎች ወይም 207 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከመመሪያ ውጪ ለሌላ አካል በህገ ወጥ ተላልፎ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

በዚህም የመንግስት መሬት በህገ ወጥ መንገድ ሲያዝ በቸልተኝነት፣ በጥቅም ትስስር መሬት እንዲወረር ያደረጉ አመራሮች፣ ባለሞያዎች እና ሌሎች አካላት ተለይተው በየደረጃው ተጠያቂ ማድረግ ስራ መጀመሩን አቶ ጥራቱ በየነ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2013 መጀመሪያ አደረግኩት ባለው የማጥራት ስራ ከ1 ሺህ ሄክታር በላይ የመንግስት ቦታዎች ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ቢያደርግም፣ 383.3 ሄክታር መሬት በድጋሚ መብት በሌላቸው አካላት እንደተያዘ እና በድጋሚ የማስመለስ ስራ ሠርቻለሁ ብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img