Sunday, November 24, 2024
spot_img

የሕወሃት ቃል አቀባዩ ዛሬውኑ ከመንግስት ጋር ለመደራር ቁርጠኛ ነን አሉ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጥቅምት 3፣ 2014 ― የሕወሃት ቃል አቀባይ የሆኑት ፍሰሃ አስገዶም ዛሬውኑ ከመንግስት ጋር ለመደራር ዝግጁ ነን ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡ ከሚድያው ጋር በነበራቸው ቆይታ ማን ያደራድር የሚለው ሁለተኛ ጉዳያችን ነው ያሉት ፍስሃ አስገዶም፣ ‹‹ለመደራደር ቁርጠኛ ነን›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በቀደመው ጊዜ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ የነበሩት ፍስሀ፣ በአሁኑ ጊዜ የአገር መከላከያ ሠራዊት ከአማራ ክልል ኃይሎች ጋር በመሆን በጦር ጄት፣ በድሮን፣ በታንክና በሌሎችም ከባድ መሳሪያዎች የታገዘ ጥቃት እየተፈጸመብን ስለሆነ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አንድ ነገር ያድርግ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፍስሃ አስገዶም የአሁኑ የመከላከያ እቅድ በሦስት ሳምንታት ውስጥ መቐለን ዳግም መቆጣጠር መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ እንደተከበቡ በመግለጽም ‹‹ራሳችንን ለማዳን እየተዋጋን ነው›› ሲሉም እንገኝበታለን ያሉትን ሁኔታ ገልጸዋል፡፡

ከከፌዴራል መንግስት በኩል የሕወሃት ቃል አቀባዩ ስለተናገሩት ጥቃትን አስመልክቶም ይሁን ስለ ድርድር የተሰጠ ምላሽ የለም።

በሌላ በኩል ቃል አቀባዩ የሕወሃት ኃይሎች በተቆጣጠሯቸው የሰሜን ወሎ እና ጎንደር ጥቃት እያደረሱ ነው በሚል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀረበባቸውን ጉዳይ ‹‹ይህ የኛ ጠባይ አይደለም›› ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

በቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካው ቃለ ምልልስ ፍስሃ አስገዶም ከሰሞኑ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እረፍት ውጡ የተባሉትን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) የኢትዮጵያ ኃላፊ የሆኑት ማውሪን አቺየንግን በተመለከተም የተናገሩ ሲሆን፣ ቃል አቀባዩ የመንግስታቱ ድርጅት በኃላፊዋ ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ ደግፈውታል፡፡ ፍስሃ ኃላፊዋን የፌዴራል መንግስት ካድሬ ምግባር አሳይተዋል ሲሉ ከሰዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img