Sunday, October 6, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፌስቡክ ገጹ ከቁጥጥሩ ውጭ ወጥቶ እንደነበር አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ መስከረም 28፣ 2014 ― የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፌስቡክ ገጽ በዛሬው እለት ለተወሰነ ጊዜ ከቁጥጥሩ ውጭ ወጥቶ እንደነበር አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ የፌስቡክ ገጹ ከቁጥጥሩ ውጭ ወጥቶ በነበረበት ሰዐት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ የተላለፈ ነው የተባለ ሐሰተኛ መልዕክት ተለጥፎ እንደነበር ተገልጧል፡፡

እንደ አየር መንገዱ ከሆነ ዋና ስራ አስፈጻሚው በኢትዮጵያ አየር መንገድ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይሁን በሌላ መንገድ ያስተላለፉት ምንም አይነት መልዕክት አልነበረም። ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ በነበረው የፌስቡክ ገጽም ተለጥፎ የነበረው መልዕክት የዋና ስራ አስፈጻሚውንም ሆነ አየር መንገዱን እንደማይወክል አስታውቋል።

ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ የነበረውን የፌስቡክ ገጽ በአሁኑ ሰዐት በአየር መንገዱ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝም ነው የተገለጸው፡፡

በሳምንቱ መጀመሪያ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የፌስቡክ ገጽ ሐክ መደረጉ መነገሩ አይዘነጋም፡፡  

የብሔራዊ ተቋሙ ሚዲያ ሐክ ተደርጓል በተባለበት ሰአት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕወሓት ጋር ድርድር እናደርጋለን የሚል መልእክት በእለቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አድርጎታል በተባለ ‹‹የዝግ ስብሰባ›› ላይ መናገራቸውን የሚገልጽ ዜና ተጋርቶ ነበር፡፡

የጣቢያው የፌስቡክ ገጽ ከጥቂት ቆይታ በኋላ መልሶ በቁጥጥሩ ስር እንደገባም ተገልጧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img