Sunday, November 24, 2024
spot_img

ዶ/ር ስለሺ በቀለ የሕዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪ እና አማካሪ ተደርገው ተሾሙ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 27፣ 2014 ― የቀድሞው የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ተደርገው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት ከዶክር ስለሺ በቀለ በተጨማሪ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡ ከነዚህ መካከል አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን፣ ለከፍተኛ የኃላፊነት መደቦችም በሚኒስቴር ማእረግ ሹመቶች ሰጥተዋል፡፡

በዚህም በሥነ አእምሮ ሕክምና እና አነቃቂ ንግግሮች የሚታወቁት ዶ/ር ምህረት ደበበን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት፣ አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌን በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ፣ ዶ/ር ለገሰ ቱሉን በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ እንዲሁም የቀድሞን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህን በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ አድርገዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የቀድሞ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍሰሃ ይታገሱ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሲደረጉ፣ አቶ አብዱራህማን ሩቤ ደግሞ ምክትል እንደሆኑ ተሹመዋል፡፡  

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img