Sunday, October 6, 2024
spot_img

ለሌላ የመንግስት ኃላፊነት ቢታጩ ኖሮ ‹‹አልቀበለውም ነበር›› ሲሉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ

 

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 26፣ 2014 ― በዛሬው እለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ካቢኔ በትምህርት ሚኒስትርነት የተሾሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የተሾምኩበት በትክክለኛው ቦታ ነው፣ ከዚህ ለሌላ ኃላፊነት ብታጭ አልቀበልም ነበር ሲሉ ገልጸዋል፡፡

 

ፕሮፌሰሩ ይህን ሃላፊነት እንደማገልገል ከወሰድነው ከዚህ መስሪያ ቤት ውጪ ሌላ ሃላፊነት ቢሰጠኝ አልወስድም ነበር፡፡ ትምህርት በፍቅር የሚሰራ ስራ ነው፡፡ የትምህርት ሚንስቴርም ትልቅ ተቋም ነው የተሰጠኝም ሃላፊነት ትልቅ ሹመት ነው በማለት ተናግረዋል፡፡

ሹመቱን በዛሬው እለት እንደ ሌላው ሰው ነው የሰማሁት ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ እድሜ ዘመኔን በማስተማር ስራ ላይ ነው ያሳለፍኩት፣ ምናልባት ፔዳጎጂ እንደመስፈርት ይቆጠር እንደሆነ አላውቅም ብለዋል፡፡

የአገሪቱን ቀጣይ እጣ ፈንታ ለመወሰን ሁለት ጉዳዮች ከግንዛቤ ውስጥ መግባት እንዳለባቸው ያነሱት ፕሮፌሰሩ፣ እነዚህም የአገሪቱን ፖለቲካዊ ሁኔታ ማሻሻል እና ትውልዱን በትምህርት ማነፅ ነው ብለዋል። አክለውም ላለፉት 40 ዓመታት በችግር የተተበተበው የትምህርት ዘርፍ የሚጠበቅበትን መስራት አልቻለም ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ታግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢዜማው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተጨማሪ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር በለጠ ሞላን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አድርገው ሲሾሙ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል፡፡

በዚህ የካቢኔ ሹመት የሕዳሴ ግድብን በተመለከቱ ጉዳዮ ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው የውሃና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ ሳይካተቱ የቀሩ ሲሆን፣ የቀድሞ ሚኒስትር ለሌላ አገራዊ ኃላፊነት ራሳቸውን ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዚሁ የካቢኔ ሹመት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለጥቂት ጊዜያት የመሩት ዶ/ር አብርሃም በላይ የመከላከያ ሚንስትር ተደርገው ተሹመዋል፡፡

ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረቡ እጩዎችን በ2 ተቃውሞ እና በአስር ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽቆታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img