Sunday, September 22, 2024
spot_img

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ብልጽግና ሊቀመንበሩን ለመንግሥት ሹመት እጩ ቢያደርጋቸውም ሳይቀበል መቅረቱ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 26፣ 2014 ― በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ከተሳተፉ ፓርቲዎች መካከል የሆነው ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)፣ ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ሊቀመንበሩ ዶክተር ዐብዱልቃድር አደምን ለሹመት እጩ ቢያደርጋቸውም ሳይቀበለው መቅረቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የካቢኔ አባላቶቻቸውን ባስጸደቁበት መድረክ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን በተመለከተ ባብራሩበት ወቅት ነው፡፡

ብልጽግና ፓርቲ የነእፓውን ሊቀመንበር ዶክተር ዐብዱልቃድር አደምን በእጩኘት ሊያቀርብ የነበረው ለአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ አባልነት እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ፣ ገዢው ፓርቲ ብልጽግና ያቀረበውንየሹመት ጥያቄ ያልተቀበለው በምን ምክንያት እንደሆነ የተገለጸ ነገር የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img