Sunday, September 22, 2024
spot_img

የጸጥታው ምክር ቤት ዛሬ ከሰዐት በኢትዮጵያ ጉዳይ ለአስረኛ ጊዜ ይሰበሰባል

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 26፣ 2014 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጸጥታው ምክር ቤት በዛሬው እለት ከሰዐት ላይ ለአስረኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ጉዳይ እንደሚሰበሰብ ተሰምቷል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉም የተያዘው ፕሮግራም ያመለክታል።

አንቶንዮ ጉቴሬዝ ከሰሞኑ የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ሉአላዊነትን የሚጥስና ለብሔራዊ ደኅንነት ስጋት የሚሆኑ ድርጊቶችን ፈጽመዋል ያላቸውን ሰባት የተመድ ሠራተኞች ማባረሩን ተከትሎ የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ የነበሩ ናቸው።

ዋና ጸሐፊው የሠራተኞቹ መባረር ቢቃወሙም መንግሥት በአቋሙ ጸንቶ ሠራተኞቹ ኢትዮጵያን ለቀው መውጣታቸው መነገሩ ይታወሳል።

የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ጉዳይ ለዘጠኝ ጊዜያት ያህል የተሰበሰበ ሲሆን፣ የመጨረሻውን ስብሰባውን ያደረገው ባለፈው ሳምንት ዐርብ መስከረም 22 ነበር። በዚሁ ስብሰባ ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል እና የተመድ ኃላፊዎች ከኢትዮጵያ የመባረር ውሳኔ ላይ መክሮ ነበር።

ምክር ቤቱ ይህንኑ ስብሰባውን በኢትዮጵዮ ጉዳይ እንዲያደርግ የጠየቁት አሜሪካ እና ፈረንሳይን ጨምሮ ማዕቀብ እንዲጣል ጫና ቢያደርጉም፣ ቻይና እና ሩሲያ ጉዳዩን በዝርዝር ማጤን እንደሚያስፈልግ እና የትግራዩ ግጭትም የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ስብሰባው ያለ ውሳኔ ተበትኗል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤትን በተያዘው የጥቅምት ወር ጎረቤት አገር ኬንያ መምራት መጀመሯ ይታወቃል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img