Saturday, November 23, 2024
spot_img

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ ያጸድቃል

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 26፣ 2014 ― በትላንትናው እለት የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ የነበረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባውን ለዛሬ ማስተላለፉ ይታወቃል።

ሰኞ መስከረም 24 በይፋ ሥራውን የጀመረው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚኖረው መርሐ ግብር ይህንኑ ያስተላለፈውን የሚኒስትሮች ሹመትን እንደሚያጸድቅ አስታውቋል።

በዚሁ መሠረት ምክር ቤቱ በትላንትናው እለት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው በተሰየሙት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የሚቀርብለትን የካቢኔ አባላት እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ሹመት መርምሮ እንደሚያጸድቅ ነው የተነገረው፡፡

ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው የኢፌዴሪ ኘሬዘዳንት ክብርት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ሰኞ ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያቀረቡትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን ያደምጣል።

በተጨማሪም የፌዴራል መንግስት የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባርን መወሰኛ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያፀድቃል ተብሏል።

ምክር ቤቱ በመክፈቻ ስብሰባው እለት አቶ ታገሰ ጫፎን በአፈ ጉባዔነት የመረጠ ሲሆን፣ ወይዘሮ ሎሚ በዶን ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መሰየሙ አይዘነጋም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img