አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 24፣ 2014 ― በዛሬው እለት እየተካሄደ የሚገኘው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞውን የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ አገኘው ተሻገርን አፈጉባኤ አድርጎ መርጧል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገር በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መኃላ የፈፀሙ ሲሆን፣ ኃላፊነታቸውን ከቀድሞው የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ተረክበዋል።
ምክር ቤቱ በተመሳሳይ ወ/ሮ ዛህራ ኡመድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አድርጎ መርጧል።
ወይዘሮ ዛህራ የአፋር ክልል የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ የነበሩ ናቸው።