Sunday, October 13, 2024
spot_img

ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው ተሰየሙ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 24፣ 2014 ― የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ተመርጠዋል።

አቶ ታገሰ ጫፎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ

በዛሬው እለት እየተካሄደ በሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛው የምክር ቤቱ ምስረታ ጉባኤው በተጨማሪም አቶ ታገሰ ጫፎን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ መርጧል።

ምክር ቤቱ ሹመቱን ያጸደቀው ዐቢይ አሕመድ በብልጽግና ፓርቲ ለጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታ እጩ አድርጎ ካቀረበ በኋላ ነው።

የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱን ተከትሎ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከፍተኛውን የሕግ አስፈጻሚ አካል ስልጣን ይዘዋል።

በዚሁ መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአገሪቱ ርዕሰ መስተዳድር፣ የሚንስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ይሆናሉ።

ከጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ተግባራት መካከል የሚመርጧቸውን የሚኒስትሮች ምከር ቤት አባላትን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው እንዲሾሙ ያደርጋሉ።

ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ያለፉትን ሦስት ዓመታት በተመሳሳይ አገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መምራታቸው ይታወቃል።

ምክር ቤቱ በዛሬው እለት አቶ ታገሰ ጫፎን በአፈ ጉባዔነት የመረጠ ሲሆን፣ በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መኃላቸውን በመፈፀም ኃላፊነቱን ተረክበዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ወይዘሮ ሎሚ በዶን ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img