Sunday, November 24, 2024
spot_img

ኢዜማ ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ የቀረበለትን የአብረን እንስራ ጥያቄ መቀበሉን አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ መስከረም 23፣ 2014 ― የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ጉባዔውን ትላንት መስከረም 22 እና ዛሬ 23 አካሂዷል፡፡

በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ያሳለፈው ፓርቲው፣ ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ የቀረበለትን የአብረን እንስራ ጥያቄ መቀበሉን አሳውቋል።

ፓርቲው ጥያቄውን የተቀበለው “ሀገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር” መሆኑን ነው የገለጸው።

በዚህ ሳምንት በተካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ ምስረታ ላይ የኢዜማ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img