Saturday, September 21, 2024
spot_img

ብሔራዊ ባንክ ብድር ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ አሻሻለ

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ መስከረም 23፣ 2014 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ከብድር አቅርቦት ጋር በተያያዘ የጣለውን ገደብ ታሳቢ ያደረገ ማሻሻያ በማድረግ፣ ባንኮች አምስት የብድር ዓይነቶችን መፍቀድ እንደሚችሉ አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንክ ዓርብ መስከረም 21፣ 2014 ለባንኮች ባስተላለፈው መልዕክት እንዳስታወቀው፣ ባንኮች የሰጡትን ብድር ለማስመለስ ሐራጅ ያወጧቸውን ንብረቶች ለመግዛት ለሚጠይቁ ገዥዎች ብድር መስጠት ይችላሉ፡፡

ብሔራዊ ባንክ ብድር ይፈቀዱ ያላቸው በሁለተኛና በሦስተኛ ወገኖች መካከል የሚደረግ ግብይትና ለባንክ ሠራተኞች የሚሰጥ አስቸኳይ ብድር መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው የመኖርያ ቤት ለመግዛት ወይም ለመገንባት ከታመነባቸውና ከፀደቁ ድርጅቶችና ከተቋም ሠራተኞች ለሚቀርቡ የብድር ጥያቄዎች፣ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት የሚችሉ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች የላከው ማሻሻያ ያመለክታል፡፡

ሌላው ባንኮች ብድር መፍቀድ ይችላሉ የተባለው በጎንደር አካባቢ ለሚገኙ የሰሊጥ አምራቾች ነው፡፡ ወቅቱን የጠበቀ ሰሊጥ ለማምረት እንዲችሉ ታምኖበት በጎንደር አካባቢ ለሚገኙ አምራቾች እንዲቀርብ የፀደቀ የብድር ዓይነት እንዲለቀቅ መወሰኑንም ማስታወቁን የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ያመለክታል።

ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ባወጣው መመርያ፣ በሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ብድር እንዳይሰጥና የብድር አቅርቦትን ባንኮች ላልተወሰነ ጊዜ ብድር እንዲይዙ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡ በመመርያው መሠረት የተፈቀዱ ብድሮች ሳይቀሩ እንዳይለቀቁ ዕግድ ተጥሎባቸው ቆይተዋል፡፡ 🔴

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img