Sunday, November 24, 2024
spot_img

ኮሮና ቫይረስን ለማከም ሙከራ ላይ የነበረው መድኃኒት ተስፋ ሰጪ ውጤት አሳይቷል ተባለ

ኮሮና ቫይረስን ለማከም በሙከራ ላይ ያለው መድኃኒት ሞትን ብሎም በጽኑ ታሞ ወደ ሆስፒታል የመግባት መጠንን በግማሽ ሊቀንስ እንደሚችል ጊዜያዊ የክሊኒካል ሙከራ ውጤት አመልክቷል፡፡

ሞልነፒራቪር የተሰኘው ይህ የሚዋጥ እንክብል በኮሮና ቫይረስ ለተያዙ ሰዎችን በቀን ሁለት ጊዜ እንዲወስዱ በማድረግ ነበር የተሞከረው።

የአሜሪካው የመድኃኒት አምራች ኩባንያ የሆነው መርክ እንዳለው በሙከራው የተገኘው ውጤት እጅግ አበረታች ነው።

መድኃኒቱን በአሜሪካ ውስጥ ለአስቸኳይ ጊዜ ጥቅም ላይ እንዲውል ለማስቻል በመጪዎቹ ሁለት ሳምንት ውስጥ ለፈቃድ ሰጪው ተቋም ማመልከቻውን እንደሚያስገባም መርክ ገልጿል።

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን የህክምና ጉዳዮች ዋና አማካሪ ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ የሙከራው ውጤት “መልካም ዜና” መሆኑን ገልጸው፤ የአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር የሙከራውን ውጤት የተመለከቱ መረጃዎችን እስከሚመረምረው ድረስ ጥንቃቄ እንዲደረግ አስጠንቅቀዋል።

በባለሥልጣኑ ፈቃድ ካገኘም ሞልነፒራቪር የተሰኘው ይህ መድኃኒት ኮቪድ-19ን ለማከም የዋለ የመጀመሪያው እንክብል ይሆናል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img