Sunday, November 24, 2024
spot_img

ጋዜጠኛ ጸጋዬ ሐጎስ በዋስትና ተለቀቀ

የመንግሥታዊው ልሳን ኢትዮጵያን ሔራልድ አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ጸጋዬ ሐጎስ በዋስትና ከእስር መለቀቁ ተሰምቷል፡፡

ላለፉት 37 ቀናት በእስር ቤት ያሳለፈው ጋዜጠኛው፣ በአስር ሺሕ ብር የገንዘብ ዋስተና ከእስር መለቀቁን ጠበቃው ነግረውኛል ብሎ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ የኢትዮጵያን ሔራልድ አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ጸጋዬ ሐጎስ፣ የሕወሓት ልሳን ለሆነው ድምጺ ወያኔ መረጃ ያሾልካል በሚል ማስረጃ እንዳለው ለፍርድ ቤት ገልጾ ነበር፡፡  

ጋዜጠኛው ጸጋዬ ሐጎስ በኅዳር ወር መጀመሪያ በተመሳሳይ ለእስር ተዳርጎ ሁለት ወራት በዚያው አሳልፏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img