Friday, November 22, 2024
spot_img

አሜሪካ፣ መንግሥት የተመድ ሠራተኞች በአስቸኳይ ከአገር ይውጡ ያለበትን ውሳኔ እንዲቀለብስ ጠየቀች

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ መስከረም 21፣ 2014 ― አሜሪካ ኢትዮጵያ በተለያዩ የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት የሚሰሩ ሰባት ሠራተኞች በአስቸኳይ ከአገር እንዲወጡ ማዘዟ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው ስትል አውግዛዋለች፡፡

የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊው አንቶንዮ ብሊንክን ኢትዮጵያ ውሳኔውን እንድትቀለብስ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይህ ባይሆን ግን አገራቸው ቆራጥ ምላሽ ከመስጠት ወደኋላ አትልም ሲሉ በትዊተር አስፍረዋል፡፡ 

የዋይት ሐውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጄን ሳኪ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥትን እርምጃ ተከትሎ በሰጡት መግለጫ፤ ያልተጠበቀ ነው ያሉትን የኢትዮጵያን ውሳኔ የአሜሪካ መንግሥት አጥብቆ ይቃወማል ብለዋል።

በተመሳሳይ አዲስ አበባ የሚገኙት የዩናይትድ ኪንግደምና የጀመርን ኤምባሲዎች መንግሥት መንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች ግዛቱን ለቀው እንዲወጡ ያዘዘበት ውሳኔ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ሁለቱ ኤምባሲዎች በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት በእርዳታ ሥራ ላይ የተሰማሩት ግለሰቦች ከአገሪቱ እንዲወጡ መደረጉ ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ መንግሥት እርምጃው እንዲያጤነው ጠይቀዋል።

መንግሥት በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይን ጨምሮ ሰባቱ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ተቋማት ሠራተኞች በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል በማለት በ72 ሰዓታት ከግዛቱ ለቀው እንዲወጡ ማዘዙ የተሰማው ትላንት ከሰዐት በኋላ ነበር፡፡

ውሳኔውን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ብሊንክን ኢትዮጵያ የተቋማቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ከአገር እንዲወጡ መወሰኗ “አስደንግጦኛል” ማለታቸው መነገሩም የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img