አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 20፣ 2014 ― የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉአላዊነት ፓርቲ አመራሩ አቶ አብርሃ ደስታ በዛሬው እለት መታሠራቸው ተሰምቷል፡፡
ለጥቂት ወራት ትግራይ ክልልን ባስተዳደረው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ዋና ኃላፊ ሆነው ያገለገሉት አቶ አብርሃ ደስታ አዲስ አበባ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡
የአረና አመራሩ በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት በነበሩት ባለፉት ሁለት ቀናት ‹‹ትግርኛ መናገር እንደ ወንጀል ተቆጥሮ የትግራይ ተወላጆች ያለ ሀጥያታቸው ፍርድ ቤት ሳያውቃቸው ከያሉበት እየታፈሱ እየታሰሩ ›› ነው የሚል እንዲሁም የጦርነቱን አስከፊነት የሚገልጹ ጹቁጥጥር ስር የመዋላቸው ዜና ከመሰማቱ ከሰዓታት በፊት ደግሞ ‹‹ጦርነትን መደገፍ ባህል ሲሆን ስለ ሰላም መስበክ ነውር ይሆናል። ፀብ ካሸለመ ዕርቅ ያስነውራል። ስለ ሰላም የሚዘረጉ እጆች የተቀደሱ ናቸው። ሰላም ለሕዝባችን›› የሚል ጽሑፍ በማኅበራዊ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉአላዊነት ፓርቲ አመራሩ አቶ አብርሃ ደስታ ለምን እንደታሠሩ አእስካሁን ድረስ በፓርቲያቸውም ይሁን በመንግስት አካል የተነገረ መረጃ የለም፡፡